ኢሬቻ የሳር እና የዓደይ አበባን ሁለት መልኮች ያጣመረ፣ የተለያዩ ማንነቶችን በአንድ ያዋሃደ፣ ኅብረብሔራዊነትን የሚያንፀባርቅ፣ ከማህበረሰብ አልፎ ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ በዓል መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፎክሎር መምህር እና የኢሬቻ ጥናት ቡድን አባል የሆኑት ጥላሁን ተሊላ (ዶ/ር) ገለጹ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተባበረ ክንድ እንደተገነባው ሁሉ ኢሬቻም የአንድነትን ጉልበት የሚያሳይ የአብሮነት በዓል መሆኑን ዶ/ር ጥላሁን ተናግረዋል።
የኢሬቻ እሴት ሰላም መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ጥላሁን፤ በዓሉ ወደ አደባባይ ከመምጣቱ በፊት ሰላምን ከቤት ጀምሮ ወደ ጎረቤት ብሎም ወደ አደባባይ መድረክ ይዞ የሚያመጣ በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር በክብረ በዓሉ ላይ ሰውን ማስቀየም ኃጢአት ይዞ መመለስ ነው ተብሎ የሚታመን በመሆኑ፤ ሌላውን ማስቀደም፣ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የበዓሉ እሴት ነው ብለዋል።
ኢሬቻ ባህልን አጥንቶ ከማስቀመጥ ይልቅ ተግባራዊ አድርጎ ወደ ልማት እና ገንዘብ መቀየር እንደሚቻል ያሳየ መሆኑንም ዶ/ር አንስተዋል።
በሴራን ታደሰ
#EBCdotstream #Irreecha #Peace