በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም ባንክ ቡድን በጋራ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ካፒታል ፎረም 2025 በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል።
ፎረሙ "ክህሎቶችን መገንባት፣ ሥራዎችን ማቀላጠፍ፣ ልማትን ማፋጠን" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ነው።
የፎረሙ ዓላማ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ባለሙያዎችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን የሰው ኃይል ካፒታል ልማት ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ ስትራቴጂዎች ላይ መወያየት መሆኑ ተገልጿል።
በለሚ ታደሰ
#EBCdotstream #Ethiopia #HumanCapital