የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ እና የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዲ በዓላት አከባበርን በተመለከተ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር ውይይት አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ወቅት በሰጡት የሥራ መመሪያ፥ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ኃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ በመሆኑ ያለፉት ሁነቶች በመላው ሀገሪቱ በስኬት መጠናቀቃቸውን አንስተዋል።
በቀጣይም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ እና የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዲ በዓላትም በስኬት እንዲከበሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፀጥታ ኃይል በማሰማራት ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።
አያይዘውም፥ የበዓላቱን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የፀጥታ ኃይሉ ከሕብረተሰቡ ጋር ትስስር ፈጥሮ እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።
የኢሬቻ ባህልና እሴት ከሚፈቅደው ውጪ በማንኛውም ሁኔታ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን፣ ስለታማ፣ ተተኳሽና ተቀጣጣይ ነገሮችን ይዞ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ መምጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።
የበዓሉ ታዳሚዎችም ለፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
#EBCdotstream #EFP #Irreecha