ከተማን በዕቅድ መስራት ያስፈልጋል፤ ከተማን ስናዘምን ለልጆቻችን የሚመች እና የሚመጥን ሀገር እየሰራን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጅግጅጋ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት ከጥቂት ጊዜ በፊት ጅግጅጋን ጎብኝተው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ያየነው ጅግጅጋ ከዚህ ቀደም ካየነው በእጅጉ የተለየ ነው ብለዋል፡፡
የኮሪደር ልማት ለዜጎች ስራ በመፍጠር ቱሪዝሙን በማነቃቃት እና የሰዎችን የአኗኗር ዘዬ በማሻሻል እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሁኑን ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ 60 ኪሎሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ 10 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ 10 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መስመር እንዲሁም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ቤቶች ተገንብተው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማት መስፋፋቱን እና ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመብራት ተጠቃሚነት በአራት እጥፍ ማደጉን ጠቁመዋል፡፡
ከተሞች በፕላን ባለመገንባታቸው የችግር መንስኤ ሲሆኑ እንደሚታይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተው፤ ከተሜነት የሚያስፈልገው ለተሳለጠ አገለግሎት ነው ብለዋል፡፡
ከተማን ስናዘምን የምንሰራው የነገ የልጆቻችን መኖሪያን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡