Search

የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመረቀ

ሓሙስ መስከረም 22, 2018 98

በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
በተመሳሳይም በዓመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር አስጀምረናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ከሁሉም በላይ ፕሮጄክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም። ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ይህም ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርብልናል ነው ያሉት።
ዛሬ በሶማሌ ክልል የጀመርናቸው ከተያያዠ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ዶ/ር) የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ ብለዋል።