Search

የኢትዮጵያ ከተሞች በአዲስ የዕድገት ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ፦ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

ዓርብ መስከረም 23, 2018 30

የኢትዮጵያ ከተሞች በአዲስዕድገት ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ ሲሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ / ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።

ከለውጡ በኋላ በከተማ ልማት ዘርፍ የሚያስደምሙራዎች እየተከናወኑ ስለመሆኑ አንስተው፤ የሀገሪቱ ከተሞች በከፍተኛ ደረጃ እየተነቃቁ እናርስ በርስ እየተወዳደሩ ይገኛሉ ብለዋል።

68 የኢትዮጵያ ከተሞች በኮሪደር ልማት በአዲስ የዕድገት ምዕራፍ ላይ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ከተሞቹ ሙሉ በሙሉ ገጽታቸው የተቀየረ መሆኑንም ነው ያከሉት።

"ከተማ ትውልድን ይገነባል፤ ትውልድ ደግሞ ከተማን ይገነባል" ያሉት / ጫልቱ፤ ከተማ ንጹህ እና ሳቢ ሲሆን ለትውልዱ ዕድገት እና አኗኗር ምቹ እንደሚሆን ገልጸዋል።

የከተሞችን ፕላን ከማስጠበቅ እና የጋራ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አኳያም በርካታ  ሥራዎች እንደተከናወኑም ነው የተናገሩት።

በመሆኑም ኮሪደር ልማትን ባህል በማድረግ ትናንሽ ከተሞች ጭምር በየአቅማቸው ከተማቸውን እያስዋቡ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁሉም ከተሞች ባላቸው ተፈጥሮ እና ሀብት ልክ መገለጥ የሚችሉበትን ሂደትን እያሳዩ ስለመሆናቸውም ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት።

በሜሮን ንብረት

#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #Cities #CorridorDevelopment