Search

‎ኢሬቻ መገፋፋት ጠፍቶ አብሮነት እንዲጎለብት ሚና እየተጫወተ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

ዓርብ መስከረም 23, 2018 38

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የ2018 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢሬቻ በዓል የይቅርታ፣ የሠላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት በዓል ነው ያሉት አቶ አሻድሊ፣ በዓሉ ጨለማው አልፎ ብርሃን፣ የችግር ጊዜ አልፎ ደስታ እና ተስፋ መተካቱ የሚዘከርበት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ ቂም፣ ጥላቻ እና መገፋፋት ጠፍቶ ወንድማማችነት እና አብሮነት የበለጠ እንዲጎለብት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የኢሬቻ በዓል ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ፤ የበለጠ እንዲተዋወቅ እና በአግባቡ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የአብሮነት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #Irreecha