የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የ2018 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፥ የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ባህል፤ እምነት እና ማንነት ልዩ ስፍራ ያለው፤ ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊ እና ምጣኔሃብታዊ እሴቶችን ያቀፈ፤ በአብሮነት እና በአንድነት በድምቀት የሚከበር ታላቅ የምስጋና በዓል ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
ባህላዊ ሥርዓቱን እና ትውፊቱን ጠብቆ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፤ ከፈታኙ የክረምት ጭጋግና ጨለማ ወደ ብርሃናማው ፀደይ ላሸጋገረ፤ ልምላሜ እና ብሩህ ተስፋን ላጎናጸፈ ፈጣሪ በኅብረት ወደ መልካ (ወንዝ) ተወጥቶ ምስጋና በማቅረብ የሚከበር የመሻገርና የብሩህ ተስፋ ምልክት ነው ብለዋል።
ኢሬቻ የሰላም እና የወንድማማችነት መገለጫ በመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በጋራ የሚያከብረው፤ አብሮነት እና ወንድማማችነት የሚጎለብትበት፤ ኅብረ-ብሔራዊነት የሚያብብበት፤ ዕርቅ እና ይቅርታ ወርዶ ሰላም የሚነግስበት እና የሕዝቦች ትስስር ይበልጥ የሚጠናከርበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #Irreecha