የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ምስጋና ማቅረቢያ፣ ተስፋን ማብሰሪያ፣ ፍቅርን እና እርቅን ማንፀባረቂያ ለሆነው ለኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የኢሬቻ በዓል፣ የኦሮሞ ብሔር በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ከሚያከብራቸው የአደባባይ በዓላት መካከል ቀዳሚው መሆኑን ጠቅሰው፣ ክረምቱ ተጠናቅቆ፣ ብራው በሚተካበት እና የተስፋ እና የመታደስ መንፈስ በሚበረታበት ወቅት የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ፈጣሪን ማመስገኛ፣ የአብሮነት እና የተስፋ ሐሴትን መጎናጸፊያ እንደሆነ ገልጸዋል።
ምድር በተፈጥሮ ፀዳል፣ በአደይ አበባ ፈክታ በደመቀችበት ወቅት የሚከበረው ኢሬቻ፣ ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረቢያ፣ ንፉግነትን እና ጥላቻን ማከሚያ ትውፊት ሆኖ የሚያገለግል እሴት ነው ሲሉም አክለዋል።
#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ