የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ የ2018 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሃጂ አወል በመልዕክታቸው፥ ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ እና የአብሮነት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ የኦሮሞ ሕዝብ ከተቀሩት የኢትዮጵያውያ ሕዝቦች ጋር በመሆን በፍቅርና በአንድነት የሚያከብሩት በዓል መሆኑን አክለዋል።
የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ልዩ የሚያደርገው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በህብረት ባሳካን ማግስት የምናከብረው መሆኑ ነው ብለዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ