Search

ኢሬቻ በአብሮነት እሴት የዳበረ በዓል ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ

ዓርብ መስከረም 23, 2018 33

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፥ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምት በፀደይ መተካቱን፣ የዝናብ ወራት አልፎ ብርሃን መምጣቱን በማስመልከት በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በጋራ የሚያከብረው ደማቅ የአደባባይ በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ፍሬ ሊያፈራ በአበባ ደምቆ፣ አዝመራው አሽቶ ፈጣሪ ፍጡራንን በመመገቡ የሚመሰገንበት በደስታ የሚከበር በዓል ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

በዓሉ የተስፋ፣ የትብብር እና የአብሮነት መንፈስን የሚያጎናፅፍ በመሆኑ የኢትዮጵያ ወንድማማች ሕዝቦች በጋራ ያከብሩታል።

ተስፋ እና ዕድል ልክ እንደ ቄጠማ በሚያብቡበት፤ ኩሬዎች እና ምንጮች እንደ መስታወት በሚጠሩበት፤ ሣር፣ ቅጠል እና ሐመልማሎች በሚለመልሙበት ወቅት ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ነው ያሉት።

#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ