የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፥ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ኢሬቻ መልካ በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና አደረሰን፣ አደረሳችሁ ብለዋል ከንቲባ ከድር።
የኦሮሞ የምስጋና ሥርዓት ደምቆ የሚታይበትን ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር፥ የኢሬቻ ዋነኛ እሴት የሆኑትን ሰላም፣ ምህረት እና አንድነትን አጥብቀን መያዝ ይገባናል ብለዋል።
በቀጣይ የሀገራችንን ማንሠራራት የሚያረጋግጡ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንድንችል ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁመን በበለጠ ትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም መልካም የኢሬቻ በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ