የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ለመላው የኢሬቻ በኛልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፥ ኢሬቻ ጨለማው የክረምት ወራት አልፎ ወደ ብሩህ ወቅት የመሸጋገሪያ ድልድይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዓሉ ፈጣሪ ለሰጠን በረከት እና ለዋለልን ውለታ ምስጋና የምናቀርብበት ነው ብለዋል።
ኢሬቻ ከምስጋና ባሻገር የፍቅር፣ የሠላም፣ የይቅርታ እና የአንድነት ጥልቅ ተምሳሌት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በኢሬቻ ልዩነቶች ይረሳሉ፤ ቂም እና በቀል በፍቅር ይተካሉ፤ ይቅርታም ይሰፍናል" ብለዋል።
የኢሬቻን የይቅርታ መንፈስ በመላ ሀገሪቱ በማስፈን ለዘላቂ የሠላም ግንባታ በተገቢው መልኩ መጠቀም ይገባልም ብለዋል።
በዓሉ ሠላምን የምናፀናበት፣ ፍቅርን የምናበለጽግበት፤ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት እጅ ለእጅ ተያይዘን የብልጽግና ጉዟችንን የምናሳካበት እንዲሆን ተመኝተዋል።
#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ