Search

የኢሬቻ በዓል በዓለም ቅርስነት ሊመዘገብ መስፈርቱን አሟልቶ አልፏል

ዓርብ መስከረም 23, 2018 40

መቻቻል፣ የአብሮነት እና የእርቅ በዓል የሆነውን ኢሬቻ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ሊመዘገብ መስፈርቱን አሟልቶ ማለፉ ተገለጸ።

የገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ሰፊ ሥራ ሲከናወን መቆየቱን የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ማርኬት ማህበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር አስማ መፍቱ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ያሉንን ቱባ እሴቶች አውጥተን ለዓለም ማሳየት አለብን ያሉት ዳይሬክተሯ፤ የኢሬቻ በዓል ባህላችንን ለዓለም የምንገልጥበት ኅብረ-ቀለማችን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ለኢትዮጵያቱሪዝም ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅዖ ያለው የኢሬቻ በዓል ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጎብኚዎች የሚሳተፉበት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ቱሪዝም የሚነቃቃበት እንደሆነም አንስተዋል።

የአብሮነት፣ የእርቅ እና የመተሳሰብሴታችን ለሚታይበት የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሰን በማለትም ዳይሬክተሯ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በሔለን ተስፋዬ

#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ