የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ በመልዕክታቸው፥ የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
ኢሬቻ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር አንድነትን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።
ኢሬቻ ከልዩነት ይልቅ አንድነት የሚንፀባረቅበት፣ የምስጋና እና የእርቅ በዓል መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልጸዋል።
ኢሬቻ ወንድማማችነትና አብሮነት የበለጠ እንዲጎለብት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመው፤ በዓሉ የበለጠ እንዲተዋወቅና በአግባቡ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ