Search

ኢሬቻ ድንቅ የሰላም ግንባታ ተምሳሌት ነው - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ዓርብ መስከረም 23, 2018 34

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ደስታ በመልዕክታቸው፥ ኢሬቻ በክረምቱ የወንዞች ሙላት ምክንያት ተቆራርጠው የነበሩ ቤተ ዘመዶችና ልዩ ልዩ ጓደኛሞች የሚገናኙበት ነው ብለዋል፡፡

በዓሉ ፀበኞች የሚታረቁበት፣ የተጣሉ ቂም እና ቁርሾ ትተው ይቅር የሚባባሉበት ድንቅ የሰላም ግንባታ ተምሳሌት ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

የኢሬቻ በዓል ሁሉም ሕዝቦች የኃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸው እንደ አንድ አባት ልጆች መሆናቸው የሚገለጥበት ስፍራ ነው ብለዋል።

ሁላችንም ከዚህ በዓል እሴቶች በመማር የእርስ በርስ መገፋፋትን አስወግደን አንድነታችንን በማጠናከር ዘላቂ ሰላም ማስፈን ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።  

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት እንዲሆን ተመኝተዋል።

#EBC #Irreecha #Ethiopia #ኢሬቻ