የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት የካቢኔ አባላት ሽግሽግ እና ምደባ ማድረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ መንግሥት በአደረገው ሽግሽግ እና ምደባ መሰረት ፦
1. አቶ አሰፋ ፎና - የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ጎሳዬ ጎዳና - የመንገድ ልማትና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
3. ዮሐንስ ዮና (ዶ/ር) - የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ መንግሥቱ ማቴዎስ - የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ብሪክ ሰለሞን - የከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ አሻግሬ ጀምበረ - የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል።