ኢሬቻ ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኘን ፀሎት የሚስተናገድበት አስደናቂ ክብረ በዓል ነው ሲል አርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ (ዲሽታጊና) ለኢቢሲ ገልጿል፡፡
የኢሬቻ ክብረ በዓል ታዳሚዎች በምድራችን ሰላም እና ፍቅር እንዲሰፍን እርጥብ ሳር ይዘው ፈጣሪያቸውን ሲለምኑ አይቻለሁ ያለው አርቲስቱ፤ አባቶች ለትውልዱ ያስተላለፉት የፍቅር፣ የአንድነት እና የሰላም ክብረ በዓል ነው ብሏል።፡
ይህንን ውብ ባህል ሁሉም በጋራ የሚያከብረው በመሆኑ ለትውልድ ማስተላፍ እና ቀጣይነት እንዲኖረው መሥራት አስፈላጊ መሆኑንም ነው የተናገረው፡፡
በንፍታሌም እንግዳወርቅ