Search

‎የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተከብሯል - የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

ቅዳሜ መስከረም 24, 2018 56

በርካታ ታዳሚዎች፣ ልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የታደሙበት "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ የተከበረው የዘንድሮ የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ዕሴቱን በጠበቀ ሁኔታ በስኬት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በያዝነው አዲስ ዓመት በርካታ ሕዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው ኃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላት በፍፁም ስኬት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል ብሏል፡፡
ለዚህ ስኬት አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም በየእርከኑ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት መምሪያው በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ስም ምስጋናውን አቅርቧል።