Search

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረበዓል በደመቀና ባማረ ሁኔታ ተጠናቅቋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቅዳሜ መስከረም 24, 2018 161

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረበዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ክብረ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ አገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንደተጠናቀቀም ነው በማሕበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት የጠቆሙት።
በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችዉ አዲስ አበባ ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት መሆን እንደቻለችም አንስተዋል።
በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ሁሉ ፣ በተለይም ለከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋናም አቅርበዋል ከንቲባዋ።