በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የኢሬቻ በዓል በኢፌዲሪ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ። 
በወቅቱም በጅቡቲ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ም/ሚሲዮን መሪ ከበደ አበራ በበዓሉ ላይ ለመታደም ለተገኙ ተሳታፊዎች እንኳን የሰላም፣ የአብሮነትና የምስጋና በዓል ለሆነው የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በማለፉና ከዘመድ አዝማድ ጋር መገናኘት በመቻሉ በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል።

በዓሉ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጅቡቲም በድምቀት ተከብሯል።
በሥነ ሥረዓቱ ላይ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በመገንባት ላይ ላለው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ድጋፍ የሚሆን የሀብት ማሰባሰብ መርሐ ግብርም መካሄዱ ተገልጿል።
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            