Search

አርሰናል የሊጉ መሪ የሆነበትን ውጤት አስመዘገበ

ቅዳሜ መስከረም 24, 2018 90

በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኢምሬትስ ከዌስትሀም ዩናይትድ የተጫወተው አርሰናል 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡

 

ደክለን ራይስ የቀድሞ ክለቡ ላይ እና ቡካዮ ሳካ በፍጹም ቅጣት ምት ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

 

እንግሊዛዊው አጥቂ ቡካዮ ሳካ በሊጉ 200ኛ ጨዋታውን ሲያደርግ 100 ግቦች ላይ ቀጥታ ተሳትፎ ያደረገበት ሆኗል፡፡

 

የ24 ዓመቱ ሳካ 55 ግቦችን ሲያስቆጥር ለ45 ግቦች መገኘት ምክንያት ሆኗል፡፡

 

ከጨዋታው ሦስት ነጥብ ያገኙት መድፈኞቹ በ16 ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምረዋል፡፡

 

በጨዋታው አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ በመጀመርያው ግማሽ በገጠመው የጉልበት ጉዳት ተቀይሮ ከሜዳ ውጥቷል፡፡

 

በአንተነህ ሲሳይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: