Search

ማንችስተር ዩናይትድ በባከነ ሰዓት ባስቆጠረው ግብ አሸነፈ

እሑድ ጥር 24, 2018 96

በ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሀምን 3 ለ 2 በማሸነፍ 3ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ካስሜሮ እና ማቲያስ ኩኛ እንዲሁም ተቀይሮ የገባው ቤንጃሚን ሼሽኮ በባከነ ሰዓት ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
ራውል ሂሚኔዝ በፍጹም ቅጣት ምት እና ኬቪን የፉልሀምን ግቦች አስገኝተዋል፡፡
ከሩብን አሞሪም ስንብት በኋላ ክለቡን የተረከበው ማይክል ካሪክ ያደረጋቸውን ሦስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ፉልሀም በውድድር ዓመቱ ለ10ኛ ጊዜ የተሸነፈበት ሆኗል፡፡
 
በአንተነህ ሲሳይ