በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ከቼልሲ የተጫወተው ሊቨርፑል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ሞይሰስ ካይሴዶ እና ተቀይሮ የገባው ኢስቲቫኦ የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
የ18 ዓመቱ ብራዚላዊ ኢስቲቫኦ በቼልሲ መለያ በሊጉ የመጀመርያ ግቡም ሆኖ ተመዝቧል፡፡
ኮዲ ጋክፖ የሊቨርፑልን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡
በመጀመርያዎቹ አምስት ጨዋታዎች ከ80 ደቂቃ በኋላ በሚያስቆጥራቸው ግቦች ሲያሸንፍ የነበረው ሊቨርፑል ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ በተቃራኒው በባከነ ሰዓት በሚቆጠሩበት ግቦች ለመሸነፍ ተገዷል፡፡
ባለፈው ሳምንት በፓላስ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ በጋላታሳራይ የተሸነፈው ሊቨርፑል ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ የተሸነፈበት ሆኗል፡፡
በሊጉ በ2 ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፈው የመርሲሳይዱ ክለብ መሪነቱን ለአርሰናል አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ