Search

ኢቢሲ የፓርላማ ቻናልን መክፈቱ የሀገሪቱን የዕድገት ጉዞ ለማፋጠን እየሠራ ለመሆኑ ማሳያ ነው - አፈ ጉባኤ መሰረት ማቲዎስ

እሑድ መስከረም 25, 2018 34

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል የሕዝቡን የመረጃ ተደራሽነት ለማስፋት ትልቅ አስተዋፅዖ የሚያበረክት መሆኑን የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ ገልፀዋል።
ቻናሉ መከፈቱ የሚረቀቁ፣ የሚፀድቁ እና የሚሻሻሉ ሕጎች እና አዋጆች ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖር ያስችላል ሲሉም ተናግረዋል።
አንጋፋው ኢቢሲ የፓርላማ ጉዳዮችን በይበልጥ ወደሕዝብ ማቅረቡ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤዋ፤ ይህም ተቋሙ የሀገሪቱን የዕድገት ጉዞ ለማፋጠን ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።
ራሱን በይዘትና አቀራረብ እያዘመነ የመጣው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2018 የኢቲቪ ፓርላማ ቴሌቪዠን ቻናሉን በይፋ ሥራውን ያስጀምራል።
 
በሚፍታህ አብዱልቃድር