የአፋር ክልል ጤና ቢሮ በአብአላ ከተማ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል አስመርቆ ሥራ አስጀመረ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብ የደም ባንክ ማዕከሉ ለአካባቢው የጤና አገልግሎት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።
በአካባቢው ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ በመሆኑ የደም ባንክ አገልግሎት ጥያቄው በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን ላይ የኅብረተሰቡ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን አቶ ያሲን ተናግረዋል።
የደም ባንክ አገልግሎቱ በዞኑ የሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች እና ለስምንት ወረዳዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
በቀጣይም በደም እጥረት ሳቢያ አንድም ሰው እንዳይሞት የደም ልገሳ መርሃ-ግብርችን በማስፋት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
በተያያዘ የአፋር ክልል ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለ100 አካል ጉዳተኞች የመንቀሳቀሻ ዊልቸር ድጋፍ አድርጓል።
በሁሴን መሃመድ