ሕዝብና ምክር ቤቱ መረጃ የሚለዋወጡበት የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የራሱን ድርሻ ለመወጣት ያስችላል ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለፁ።
የፓርላማ ቴሌቪዥን የምክር ቤቱን የሕግ አወጣጥ ሂደት፣ በምክር ቤቱ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን እና የሕዝብ ውክልና ሥራዎችን አፈፃፀም ለሕዝብ ለማቅረብ አጋዥ ነው ብለዋል።
ከዚህ አኳያ ፓርላማው የራሱ ቻናል እንዲኖረው የምክር ቤቱ የበላይ አመራሮች ከፍተኛ ቁርጠኝነት ማሳየታቸውንም አንስተዋል።
ራሱን በይዘትና አቀራረብ እያዘመነ የመጣው ኢቢሲ፤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2018 የኢቲቪ ፓርላማ ቴሌቪዠን ቻናሉን በይፋ ሥራውን ያስጀምራል።