የሕዝብ እንደራሴዎችን ሚና ለማጎልበት እና ሕዝብ የሚደመጥበትን የዴሞክራሲ ባህል ለማሳደግ የኢቢሲ ፓርላማ ቻናል መከፈት ፋይዳው የጎላ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ተናገሩ።
ሚዲያ በሕዝብ እና በመንግሥት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው፤ የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች ተጨማሪ አቅም ይሆናል ብለዋል።
የዚህ ትውልድ አካል ሆነው የፓርላማ ቻናል መከፈቱ አስደስቶኛል ሲሉ ዋና አፈ ጉባኤው ተናግረዋል።
ራሱን በይዘትና አቀራረብ እያዘመነ የመጣው ኢቢሲ፤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2018 የኢቲቪ ፓርላማ ቴሌቪዥን ቻናሉን በይፋ ሥራውን ያስጀምራል።
በተመስገን ተስፋዬ