Search

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል የለውጥ ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ነው - አፈ ጉባዔ አስካለች አልቦሮ

እሑድ መስከረም 25, 2018 33

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ለሕዝብ አማራጭ መረጃን ይዞ የመጣ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ገለፁ።
በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነው ኢቢሲ ፍትሐዊ የመረጃ ተደራሽነትን በማሳደግ የዜጎችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አፈ ጉባዔዋ ተናግረዋል።
ኢቢሲ ማኅበረሰቡ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመታገዝ ሀሳቡን በነፃነት የሚያንፀባርቅበትን ዕድል ፈጥሯል ያሉት አፈ ጉባዔዋ፤ የፓርላማ ቻናልም ለሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ሲሉ አስረድተዋል።
የፓርላማ ቻናሉም ለሕዝቡ ወቅታዊ የምክር ቤታዊ መረጃዎችን ለማድረስ የሚያስችል በመሆኑ ኢቢሲ ሊመሠገን ይገባዋል ሲሉ አፈ ጉባኤዋ ገልፀዋል።
በጀማል አህመድ