በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አንድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የምድቡን 9ኛ ጨዋታ ከጊኒ ቢሳው ያደርጋል።
ከ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ውጭ መሆኑ ቀድሞ የተረጋገጠው ብሔራዊ ቡድኑ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በሩዋንዳ የሚያደርገው ጨዋታ ከመርሀ ግብር ማሟያነት ያለፈ ትርጉም አይኖረውም።
ከቀናት በፊት ወደ ሩዋንዳ ያመሩት ዋልያዎቹ ትላንት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ጨዋታው በሚደረግበት አማሆሮ ስቴዲየም ሰርተዋል።
ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈው ብሔራዊ ቡድኑ በ6 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬ ተጋጣሚው ጊኒ ቢሳው በ10 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የምድቡ አሸናፊዎች በቀጥታ በ2026ቱ ዓለም ዋንጫ በሚሳተፉበት ማጣሪያ ምድቡን ግብጽ በ20 ነጥብ እየመራች ሲሆን ዛሬ ቀድማ ከተሰናበተችው ጂቡቲ የምታደረገውን ጨዋታ ካሸነፈች ማለፏን ታረጋግጣለች።
በአንተነህ ሲሳይ
#ebcdotstream #ebcsport #Ethiopianationalteam #WCQ