የቀድሞው የአርሰናል የቀኝ ተከላካይ ባካሪ ሳኛ ዛሬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን (ኢቢሲ) ጎብኝቷል።
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ቆይታ እያደረገ የሚገኘው ፈረንሳዊው ኮከብ በኢቢሲ ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት ዘመናዊውን የኢቢሲ የቴሌቪዥንን እና የሬዲዮ ስቱዲዮዎች ጎብኝቷል።
ኢቢሲ ባሉት ዘመናዊ ስቱዲዮዎች መገረሙን የተናገረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ተቋሙ ያለበት ቦታ ፍጹም ደስ የሚል መሆኑንም ገልጿል።
ባካሪ ሳኛ በኢትዮጵያ ያለውን ቆይታ እና የእግር ኳስ ህይወቱን በተመለከተ ከኢቢሲ ጋር ያደረገውን ቆይታ በቀጣይ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።
በአንተነህ ሲሳይ