Search

ዜጎች ከደላላ ሰንሰለት ተላቅቀው መንግስት ባዘመነው አገልግሎት ሊጠቀሙ ይገባል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ረቡዕ መስከረም 28, 2018 119

ዜጎች ከደላላ ሰንሰለት ተላቅቀው መንግስት ባዘመነው የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት እንዲገለገሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቦሌ ቅርንጫፍን በዛሬው ዕለት ሥራ አስጀምረዋል፡፡
ማዕከሉ 12 የከተማ አስተዳደር እንዲሁም 3 የፌደራል ተቋማትን በመያዝ 96 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች የሚሰጥ ነው፡፡
ከንቲባዋ የማዕከሉን አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅት፣ በከተማችን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን ቀጥለናል ብለዋል።
መንግስት የተገበራቸው የልማት ሥራዎች ውጤታማነት የሚለካው በቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ መሆኑን ገልጸው፤ ዜጎች መንግስት ባቀረበውና እንግልትን በሚቀንሰው ማዕከል በመገልገል ለብልሹ አሰራሮች ተጋላጭ እንዳይሆኑ አሳስበዋል።
በሕይወት አበበ