በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ቢሳው የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ራምኬል ጀምስ በ27ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል።
በውጤቱ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ 9 ነጥቦችን በመያዝ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ሩዋንዳ ኪጋሊ በሚገኝ ስታዲየም ነው የተጫወተው።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ