ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶስት ወራት በፊት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ጎብኝተው በገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ሞዴል የገጠር መንደሮችን ጨምሮ ዓመታዊውን የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር አስጀምረው ነበር።
በጉብኝታቸው ወቅት የሀምበሪቾ ተራራ 777 ደረጃዎች ወጥተው ለዞኑ አስተዳደር ደረጃዎቹን ጨምረው እንዲገነቡ የቤት ሥራ ሰጥተው እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውሷል።
በሶስት ወራት ውስጥ የቤት ሥራውን አከናውነው የሀምበሪቾ ተራራ ዳግም 777 ክፍልን እውን አድርገዋል ብሏል ጽህፈት ቤቱ።
በድምሩም ከ1500 ደረጃዎች በላይ በማድረስ አስደናቂው የተራራ ላይ እይታ ድረስ መገንባቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ለክልሉ ቁርጠኝነት እና ውጤት እውቅና ለመስጠትም ጠቅላይ ሚኒስትር ከመደመር መንግሥት ሽያጭ የተገኘ ገቢን በሀምበሪቾ ተራራ ሥር የማረፊያ ግንባታ ይገነባ ዘንድ ስጦታ ማበርከታቸው ተመላክቷል።
ይኽም አካባቢው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትዕይንታዊ ቱሪዝም መዳረሻነት መጎልበት የበለጠ የሚያገለግል ይሆናል ተብሏል።
#EBC #ebcdotstream #PMO