ሀገር አቀፍ ሞዴል የእንስሳት አርቢዎች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ተከብሯል።
በወቅቱም የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ሥራዎችን ጎብኝተው፤ የእንስሳት መኖ ተከላን አስጀምረዋል።
በወላይታ ዞን በወተት ላሞች እርባታ የታየው ተሞክሮ የሚበረታታ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ውጤታማነቱን ይበልጥ ለማሳደግ ሥራውን ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በእንስሳት እርባታ እና በሌማት ትሩፋት የታየውን ለውጥ ለማስፋፋት ይሰራል ብለዋል፡፡
አርሶአደሮች በበኩላቸው የእንስሳት እርባታ እና የሌማት ትሩፋትን የተመለከቱ አዳዲስ ተሞክሮዎችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
በመርሃ-ግብሩ የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) እና የወላይታ ዞን የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎችን ተገኝተዋል።
በተመስገን ተስፋዬ