ሞዴል የገጠር መንደሮች የተመኘነው ብልፅግና እውን የመሆን ጊዜው ሩቅ አንዳልሆነ ማሳያ ናቸው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሞዴል የገጠር መንደሮች የነገዋ ኢትዮጵያ እና ዜጎቿ የሚኖራቸውን የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ የሚያሳዩ ናቸው ያሉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ ይህንን ለውጥ አጠናክሮ መጓዝ ይገባል ብለዋል።
የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ቀለል ባለ መንገድ ከተማ ውስጥ ያለውን የኑሮ ዘይቤ በማምጣት የተሠራዉ ሥራ የተሻለ ሕይወት መኖር አንደሚቻል ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
ብልፅግናን እናረጋግጥ ሲባል ሰው ከአኗኗሩ እና ከቤቱ መጀመር እንዳለበት እየተሠራ ያለው ልማት ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ