Search

የገጠር ሕይወትን የሚቀይሩ ውጤታማ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 29

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የተሰሩ ሥራዎችን ለማደናቀፍ ለሚሞክሩ አካላት ጊዜ እንደሌላቸው እና ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደተለያዩ አካባቢዎችም እንደሚስፋፉ ቃል ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በክልሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ መመሪያ እና ድጋፍ በመስጠት ላበረከቱት አስተዋጽኦም ርዕሰ መስተዳድሩ አመስግነዋል።
 
በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው፤ ሞዴል የገጠር መንደሮች የተሻለ ኑሮ ከተማ ብቻ ሳይሆን ገጠርም ጭምር መኖሩን ማሳያ ናቸው ብለዋል።
ይህንን ሥራ በየአካባቢው ለማስፋፋት ጥረት እንደሚደረግም ገልጸዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ