የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ እና የጤፍ ግብርና ልማት ጎብኝተዋል።
በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ20 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ከዚህ ውስጥ12.3 ሚሊዮን የሚሆነው በኩታገጠም ክላስተር የለማ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን ላይ በሀገሪቱ በስፋት እየተሰራበት የሚገኘው የኩታ ገጠም እርሻ ምርታማነትን ከ30 በመቶ በላይ ማሳደግ አስችሏል ብለዋል።
በወንድወሰን አፈወርቅ
#EBC #agriculture #Ethiopia