Search

“ኢትዮጵያውያን በክንዳችሁ ብርታት ሰንደቅ ዓላማውን መጠበቅ ይገባችኋል” - ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

ሰኞ ጥቅምት 03, 2018 141

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በተገኙበት ተከብሯል።
ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በአስተላለፉት መልዕክት፤ የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብር እና ቃልኪዳን በልቡ የሚያድስበት ክብረ በዓል ነው ብለዋል።
የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጋራ ማንነታችንን የምናፀናበት ታላቅ ክብረ በዓል ነው ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
በዓሉን ስናከብር ያለፈውን የጀግንነት ገድላችንን፤ የዛሬውን የልማት ጥረታችንን እና የነገውን የዕድገት እና የብልጽግና ውጥናችንን አጣምሮ በያዘው “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በልባችሁ የሰላምን የተስፋ ወጋገን አጥብቆ በመያዝ በክንዳችሁ ብርታት ሰንደቅ ዓላማውን መጠበቅ ይገባል ብለዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእውቀቱ ፣በጉልበቱ እና በሚችለው ሁሉ የኢትዮጵያን የእድገት ግስጋሴ በማሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ