Search

ምስጢር ጠባቂው የኖቤል ሰዓሊ

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 76

በየዓመቱ በሚካሄደው የኖቤል ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የአሸናፊዎች ስም ይፋ ሲደረግ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመለከተው ምስል የፎቶግራፍ አይደለም።
ይህ ምስል በደማቅ ጥቁር መስመሮች እና በሚያብረቀርቅ ወርቃማ ቀለም ያጌጠ ስዕል ነው።
እነዚህን ልዩ እና ታዋቂ ስዕሎችን የሚያዘጋጀው ሰው ኒክላስ ኤልመሄድ ይባላል።
 
ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ ሁሉንም የኖቤል ተሸላሚዎች ስዕል የሚሰራ ብቸኛው የኖቤል ሰዓሊ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
የኒክላስ ሥራ ከሰዓሊነትም ባለፈ ከፍተኛ ምስጢር የመጠበቅ ኃላፊነት ያለው ነው።
 
ከኖቤል ሽልማት ሰጪ ኮሚቴዎች የአሸናፊዎቹን ማንነት ቀድመው ከሚያውቁት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች አንዱ መሆን የቻለ ነው።
ኒክላስ ኤልመሄድ እስካሁን ድረስ የበርካታ የኖቤል አሸናፊዎችን ስዕል ያዘጋጀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አንዱ ናቸው።
በየዓመቱ ከሚደረገው የኖቤል ሥነ ሥርዓት በፊት የአሸናፊዎቹን ማንነት የሚያውቀው ስዊድናዊው ሰዓሊ ኒክላስ ኤልመሄድ የአሸናፊዎቹ ዝርዝር እንደደረሰው በጥቁር አክሬሊክ ቀለም እና በወርቃማ ፎይል ምስሎቹን ያዘጋጃል።
በዚህ ሥራውም ምስጢር ጠባቂው የኖቤል ሰዓሊ በመባል ዝናና ታዋቂነት አግኝቷል።
 
በዋሲሁን ተስፋዬ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: