Search

ሉሲዎቹ ከ14 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 65

የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ በዚህ ዓመት በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለ16ኛ ጊዜ ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 16 ሀገራት በሚሳተፉበት መድረክ ለመሳተፍ ከታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን የ180 ደቂቃ የደርሶ መልስ ጨዋታ ብቻ ይቀረዋል፡፡
በአንደኛው ዙር ማጣሪያ የዩጋንዳ አቻቸውን በመለያ ምት 5 ለ 4 አሸንፈው ለ2ኛው እና ለመጨረሻው ዙር ማጣሪያ የደረሱት ሉሲዎቹ የመጀመርያ ጨዋታቸውን በመጭው ረቡ ከታንዛኒያ ያደርጋሉ፡፡
የመልሱን ጨዋታ ደግሞ በአዲስ አበባ የሚያደርጉ ሲሆን በደርሶ መልስ ድምር ውጤት ካሸነፉ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአህጉሩ መድረክ መሳተፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ የሚመሩት ሉሲዎቹ ባለፉት 22 ቀናት ጠንካራ ልምምድ ሲያደርጉም ቆይታዋል፡፡
ከታንዛኒያ የሚደረገውን ጨዋታ በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ጸሃፊ ባህሩ ጥላሁን በሰጡት ሃሳብ በውጭ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾች ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ የተናገሩ ሲሆን በአሜሪካ የምትገኝው ሎዛ አበራ ግን ለመጀመርያው ጨዋታ እንደማትደርስ አሳውቀዋል፡፡ የሉሲዎቹ አጥቂ ሎዛ አበራ ለመልሱ ጨዋታ ግን እንደምትደርስ ይፋ ተደርጓል፡፡
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ ለወሳኙ ጨዋታ በሁሉም መንገድ በቂ ዝግጅት አድርገው ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡
የቡድኑ አምበል ታሪኳ በርገና በበኩሏ ታሪክ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ተናግራለች፡፡ ብሔራዊ ቡድኑም የፊታችን ሰኞ ወደ ታንዛኒያ የሚያመራም ይሆናል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: