Search

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ

ቅዳሜ ጥቅምት 08, 2018 61

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን ዐበይት ተግባራት የደረሱበት የአፈፃፀም ደረጃ እንደሚገመገም የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፤ መድረኩ የተገኙ ውጤታማ አፈፃፀሞችን ይበልጡን አልቀን በማስቀጠል እና የታዩ ጉድለቶችን በማረም እንዲሁም ትኩረት እና የተለየ ርብርብ የሚሹ ተግባራትንም ለይተን ቀጣይ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ይሆናል ብለዋል።

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #AddisAbaba