Search

የቱሪዝም መስህቦች ከባቢ መሰረተ ልማት ግንባታ የዘርፉን የገበያ ስርዓት የሚያስተካክል ነው - የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)

ሰኞ ጥቅምት 10, 2018 56

የቱሪዝም መስህብ ከባቢ መሰረተ ልማት ግንባታ የቱሪዝሙን የገበያ ሥርዓት እንደሚያስተካክል የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ገለፁ።
ለቱሪዝም መስህብነት የሚሆኑ ስፍራዎች መሰረተ ልማት መሟላት የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ የሚያራዝም እና የጎብኚዎችን ፍላጎት ያማከለ መሆኑን ገልፀዋል ሚኒስትር ዴኤታው።
ከዚህ ቀደም በነበረው ሁኔታ ቱሪስቶች መስህቦችን አይተው ብቻ እንደሚሄዱ ገልፀው፤ አሁን ግን ከማየት አልፈው ሄደው የሚያወሩት መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ አሁንም በርካታ ያልተነኩ የቱሪስት መስህቦች እንዳላት መገንዘብ እንደተቻለም ነው በቆይታቸው ያነሱት።
የቱሪዝም ፖሊሲ አንዱ ዕይታ ከዜሮ ከመጀመር ይልቅ ነባር የሀገር ሀብት ላይ እሴት መጨመር መሆኑንም አንስተዋል።
ያሉን ሀብቶች ላይ ተጨማሪ እሴት መጨመር ደግሞ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ለቱሪዝሙ ጥሩ መደላድል እንዲፈጠር ብሎም የገቢ ምንጮች እንዲያድጉ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
 
በሴራን ታደሰ