በኦሮሚያ ክልል የባሌ ዞንን በሥራ ምክንያት ብዙ ጊዜ እንደተመላለሱበት የተናገሩት የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ነገር ግን ባሌ ይህን ሁሉ ሀብት እንዳለው ያየሁት አሁን ነው ብለዋል።
ባሌ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የሚበቃ ሀብት እያለው ግን ድህነት እና የመሰረተ ልማት እጥረት ይህን ሀብት መጠቀም እንዳይቻል ማድረጉ በጣም የሚቆጭ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይህን ሀብት ይዞ በድህነት ውስጥ መኖር፣ በዚህም ምክንያት ሀገርን መገንባት የሚችሉ ወጣቶች በስደት እየተሰቃዩ መሆኑ እንደሚቆጫቸውም ተናግረዋል፡፡
አሁን ግን ዓይን ከፋች ሥራ መጀመሩን ጠቅሰው፣ መጪው ትውልድ በሀገሩ የሚኮራበትን ሥራ በሰፊው መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሃብት ባሌ ውስጥ መገኘቱን ሁሉም ማወቅ አለበት ያሉት አቶ አባዱላ፣ "በሕይወት ኖሬ እንደዚህ ዓይነት ውበት ለማየት በመቻሌ ዕድለኛ ነኝ ብዬ ነው የማስበው" ብለዋል፡፡
በለሚ ታደሰ