መልካም ታሪኮቻችን ለሀገር ግንባታ መጠቀም እና አንድነትን ተጠቅሞ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ መስፍን ዳኜ ገልጸዋል።
በብሔራዊ ጥቅም ላይ የማይደራደር ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ የገለፁት አቶ መስፍን፣ በባሕር በር ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ከነጣይ ትርክት ይልቅ የወል ትርክትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ፖለቲከኞችና ምሁራን ሀገርን አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ሀገር የሚገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ በመሆኑ የትናንት ስህተቶችን እያረሙ ለሀገር የሚመጥን አዲስ ነገር በመፍጠር ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ ሀገርን ማስተላለፍ እንደሚገባም ገልጸዋል።
በሄለን ተስፋዬ