Search

ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ትስስር ላቅ ያለ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው - ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ

ረቡዕ ጥቅምት 12, 2018 40

የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ትስስር እያደረገችው የሚገኘው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ መሆኑን ገለጹ።
ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ኢትዮጵያ ከዘመናት በፊት ጀምሮ አፍሪካዊነትን ስታቀነቅን እንደኖረችና የቀጣናውን ሰላም በማስከበር ረገድ በርካታ ሥራዎች እንደሰራች አንስተዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ኋላቀርነት ለመላቀቅ የተነደፉ ሜጋ ፕሮጀክቶች አጎራባች ሀገራትንም ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያ ዕድገትና ሰላም ለሁሉም አጎራባች አገራት ያለው ሚና ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
ሥራ አጥነትን በመቀነስ እና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማጎልበት የኢኮኖሚውን አቅም ማሳደግ እንደሚቻልም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ትስስር ያላትን ቁርጠኝነት በማጠናከር በትምህርት ዘርፍም ከሶማሊያ እና ሱዳን እና ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራትም ተማሪዎችን በመቀበል እያስተማረች መሆኑን አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የወደብ ጉዳይን አጀንዳ ማድረጓን አመላክተው፤ ይህ በቀጣይ ለቀጣናው ትስስር ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
 
በሜሮን ንብረት