ቀደም ብሎ በመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ የነበረው የባሌ አካባቢ አሁን ላይ ለጎብኚዎች ምቹ እየሆነ መምጣቱን የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ቀደምት የሀገር መሪዎች ያልሠሯቸውን ሥራዎች አሁን ያለው መንግሥት በተባበረ መንፈስ ልማቶችን ሲያከናውን ማየት በራሱ ብርታትን ይሰጣል ብለዋል።
ሀገር በእንደዚህ ዓይነት የትውልድ ቅብብሎሽ ወደፊት እንደምትራመድ መማር ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፤ እርስ በርስ ስንዋደድና ስንከባበር ሀገርን ወደፊት ይዘን መጓዝ እንችላለን ሲሉም አክለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተገነቡ እና የተጀመሩ ምቹ ማረፊያና መዝናኛ ቦታዎች፣ የመስኖ መሠረተ ልማቶች ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሃብቶችን በትክክለኛው መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።
በተከናወኑ የልማት ሥራዎችም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ምን ያህል ወደፊት ማስቀጠል እንደሚቻል መማር ተችሏል ሲሉም ተናግረዋል።
በቀጣይም በመከባበር መንፈስ በጋራ በመሥራት እና የጎደለውን በመሙላትና አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ ገለፀዋል።
በሜሮን ንብረት