የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሶስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ ምክር ቤት አባላትን ቁጥር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ በመወያየት ለምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።
2ኛ. የተቋራጭ የግንባታ ግዢና የሥራ ስምሪት የአሰራር ደንብ ላይም ተወያይቶ ወሳኔ አሳልፏል፡፡
3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ ላይ ውይይት በማድረግም ውሳኔ አሳልፏል፡፡