ኢትዮጵያ የተለያዩ ሥነ-ምህዳሮች ያሏት ሀገር በመሆኗ፣ ሀብቷን ከአርሶ አደሩ ጠንካራ ሥራ ጋር ደምራ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር ንጉሴ ደቻሳ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ከኤፍ. ኤም አዲስ 97.1 ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የምግብ ሉዓላዊነት የአካባቢ ደህንነትን በመጠበቅ በዘላቂነት የተመረተ ጤናማ ምግብን የማግኘት መብት መሆኑን ገልፀዋል።
የምግብ ሉዓላዊነት መመገብ ብቻ ሳይሆን ምግብን ለማምረት የሚያስችሉ ሃበቶችን በዘላቂነት የመጠቀም አቅም ነው ብለዋል።
የምግብ ሉዓላዊነት የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በላይ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ምግብን ከሸቀጥ አልፎ እንደመብት የማየት አቅምን የሚፈጥር እና እራስን የመቻል ትልቁ ምልክት መሆኑን ነው ያስረዱት።
ኢትዮጵያም የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እየሰራች ባለው ሥራ አመርቂ ውጤት መመልከት መጀመሯን ጠቅሰዋል።
በዚህም ሀገሪቱ በስንዴ እና በሩዝ ምርት ላይ እያሳየች ያለው እመርታ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል።
በሴራን ታደሰ