Search

9.2 በመቶ ጥቅል ዓመታዊ የምርት እድገት ያሳየው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

ሓሙስ ጥቅምት 13, 2018 30

የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈጻጸም በ2017 ዓ.ም 9.2 በመቶ ጥቅል ዓመታዊ ምርት (GDP) እድገት ማሳየቱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሯ ይህንን የገለጹት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው።
የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸሙ መሰረት ግብርና 7.3 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 13 በመቶ፣ እና የአገልግሎት ዘርፍ 7.5 በመቶ ማደጋቸውን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ በዓለም የኢኮኖሚ ልማት አውድ ውስጥ ልዩ ጥንካሬ እና የእድገት ፍጥነት ማሳየቷን ገልጸዋል።
በተለይም ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ ውጤት መታየቱን እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጪ ንግድ እድገት ያስመዘገበችበት ዓመት መሆኑንም አብራርተዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ